መንግስት ያወጣውን የአስቸኮይ አዋጅ በመቃወም ከፍተኛ ተቃውሞ በነቀምት ወለጋ ዛሬ ሲደረግ ውሎል

የአስቸኮይ አዋጁ በኢትዮጵያ ከታወጀም በሆላ የህወሃት መንግስት ያወጣውን የአስቸኮይ አዋጅ በመቃወም ከፍተኛ ተቃውሞ በነቀምት ወለጋ ዛሬ ሲደረግ ውሎል።

ቅዳሜ ሰሞኑን ከእስር ተፈተው የነበሩት በቀለ ጋርባ በፌድራል ሰራዊት መታገታቸው ታውቆል።

ይሁን እንጂ የአስቸኮይ አዋጅ በመቃወም ከፍተኛ ተቃውሞ ተከትሎ  የመንግስት ወታደሮች በአፀፋው በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ቀጥተኛ ተኩስ ማድረጋቸውን ከደረሰን ምስል ለማየት ተችሎል። በኦሮምያ እና አማራ ክልሎች የተጀመረው ተቃውሞ እንደቀጠለ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ። ይህንንም ተከተሎ በሰላማዊ ሰልፈኞች የደረሰ ጉዳት መኖሩን አረጋግጠናል።

ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል የመንግስት ወታደሮች መገደላቸውን አረጋግጠናል። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ መንግስት ያወጀው የአስቸኮይ አዋጅ የዜጎችን መብት የሚያፍን እና ዜጎች መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዳይጠይቁ የሚያደርግ ነው ሲል የአለም አቀፍ መንግስታት ማጣጣላቸው ይታወሳል።

ይህ በንዲህ እንዳለ የፂትዮጵያን ጉዳይ የሚመለከተው ረቂቅ ህግ ወደ ድምፅ ከመቅረቡ በፊት ለኢትዮጵያ መንግስት መልስ እንዲሰጥ የተሰጠው የ28 ቀናት ገደብ ሊጠናቀቅ 2 ቀናት ቀርተውታል። እስካሁን መንግስት በጉዳዩ ላይ መልስ አልሰጠም።

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*