ስለኢትዮጵያ የሰበአዊ መብት የሚመለከተው Sen.Res168 እና H.Res128 ህግ  በሁለቱም ምክርቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ አልፏል

በአሜሪካ መንግስት ሁለቱ ምክርቤቶች ስለኢትዮጵያ የሰበአዊ መብትና የዴሞክራሲ ጥሰት እስራትና ግድያ በአስቸኳይ ይቆም እና እንዲሁም እቀባ ይደረግ ዘንድ የሚመለከተው HR128 እና Sen.Res168 ህግ  በሁለቱም ምክርቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ አልፏል። ለቀጣዩ ድምፅ ወደ ሙሉው ምክርቤት ተልኳል።

የዚህ ህግ ማለፍ ከፍተኛ ጠቃሚነት ያለው ሲሆን  በተለይም ካለምንም ማናለኝበት በዜጎች ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርሰውን በደል ልጓም ሊያበጅለት ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

ረቂቅ ህጉ ከሌሎች አለማችን ከሚያሰጉ መንግስታት ጋር አብሮ የወጣ ሲሆንየደቡብ ኮሪያን፣ ሄዝቮላ፣ ኢራን፣ ቬንዙወላን እና ኢትዮጵያን ያጠቃልላል። ይህህግ ወደ ሙሉ ምክር ቤቱ ቀርቦ ከፀደቀ ለመጀመሪያ ጊዜ የአሜሪካ መንግስትበኢትዮጵያ መንግስት ቀጥተኛ የሆነ ጫና ማሳደር ትጀምራለች ተብሎይጠበቃል።

በሁለቱ ምክርቤት የቀረበው ህግ የኢትዮጵያን መንግስት ባለስልጣናትን የጉዞማእቀብና ሌሎች የገንዘብና ቁሳቁስ ታእቅቦዎችን ያካትታል።

 የዚህን ህግ አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግስት ሀገር ውስጥ ለሚታተመው በሰንደቅ ጋዜጣ  አማካኝነት ቀጥተኛ መልስ ከሁለት ሳምንት በፊት መስጠቱ የሚታወስ ሲሆን ” ረቂቅ ህጉን የአሜሪካ መንግስት የአምባገነንነትና የጠብ ጫሪነት ህግ ነው” ሲል አጣጥሎታል። አያይዘውም የዚህን ህግ አርቃቂ የአሜሪካ የህግ አውጭዎችን ባለስልጣናት ከኤርትራ መንግስት ጋር ተባብረው በኢትዮጵያ ሽብርና ትርምስ ለመፍጠር የሚሰሩ ጉልበተኞች ናቸው ሲል ንዴታቸውን ጨምረው በጋዜጣው ላይ አስፍረዋል።

በጉዳዩ ላይ ያላቸውን መልስ ወይም አስተያየት እንዲሰጡ የጠየቅናቸው የዚሁ ህግ አርቃቂ ባለስልጣናት ሲመልሱ “ይህ የአምባገነን መንግስታት ባህርያት መገለጫዎች ሰለሆነ ሊገርመን አይችልም” ሲሉ ተናግተዋል።

የሁለቱን ህጎች ረቂቅ ሃሳብ ወደ ቀጣዩ ክፍል ለመውሰድ ብዙ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን እና በዚህ ውጤት ሳንዘናጋ እስከመጨረሻው መስራት ይኖርብናል ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያን አድቮከሲ ኔትወርክና የኢትዮ አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር አርያ አምሳሉ ናቸው።

ይህ በንዲህ እንዳለ የፊታችን ሴፕቴምበር 23 እና 24 በዋሽንገትን ዲሲ በሚደረገው የራእይ ለኢትዮጵያ ስብሰባ ላይ የካውንስሉ አስተባባሪ ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ ይህን አስመልክቶ ንግግር ያደርጋሉ። በእለቱም ከአሜሪካ ምክርቤት ባለስልጣናት ተወካዮች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

8 Comments

 1. Ethiopian government had manipulated the global war on terror to violate citizens human, political and civil rights in Ethiopia that the international community need to understand such state terrorist Ethiopian government is corrupting and violating both its international and domestic commitments.

 2. ዲ/ን ዮሰፍን ከልብ ከልብ አመስግኑልኝ። እንደሳቸው ያሉ ይብዙልን ሁላችሁም ግዜያችሁን ጉልበታችሁን እና ገንዘባችሁን ሳትሰስቱ ለምታደርጉት የወደፊቷ ሰላማዊና ፍቅር የበዛባት ያደገች ኢትዮጵያ ምስረታ ምስጋናዬ የላቀ ነው። እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ።

 3. This is a very important step towards challenging the long suffering Ethiopians and a way to see the true nature of this government. I do not believe that the terriest group will stop their killing and tourturi g but at least the Freedom fighters will be recognized if this bill passes. If America and others stop supporting this government, at least it will stop pretendeding that it has the support of these governments for its own human right abuses.

 4. We support HR 128
  Because human rights violations in
  Ethiopia by its own Government
  Should be stopped as soon as possible
  Please help us to pass HR 128.

 5. We support HR128
  Because human rights violations in Ethiopia by it’s own dictatorship government killed ,torched
  Thousand of them jailed. So to stop these problem we need your support to pass HR 128
  Please we beging you again.

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*