በመጨረሻም Hres 128 ረቂቅ ህጉ ነገ ለድምፅ ይቀርባል

Hres 128ን የአሜሪካ ኮንግረስ እንዲያጸድቀው ጥሪ ቀረበ

 (ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 1/2010)በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ አስተዳደር እንዲኖርና የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ ተጽእኖ የሚያሳድረውን ኤችአር 128 የአሜሪካ ኮንግረስ እንዲያጸድቀው ስድስት የሰብአዊ መብትና የዲያስፖራ ቡድኖች ጥሪ አቀረቡ።

ኤችአር 128 በነገው እለት በአሜሪካ ኮንግረንስ ፊት ቀርቦ ድምጽ ይሰጥበታል።

ኤች አር 128 በኮንግረሱ እንዲጸድቅ ጥሪ ያቀረቡት ስድስት የሰብአዊ መብትና የዲያስፖራ ቡድኖች ናቸው።

እነሱም ሒዩማን ራይትስዎች፣ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ፕሮጀክት፣የኢትዮጵያ አድቮኬሲ ኔትወርክ፣የአማራ ማህበር በአሜሪካ፣የኦሮሞ አድቮኬሲ ትብብር፣ቅንጅት ለኦሮሞ ሰብአዊ መብትና ለዲሞክራሲ ናቸው።

ኤች አር 128 ገለልተኛ በሆኑ አካላት በእጅጉ የሚደገፍ ሲሆን እስካሁንም ከመቶ በላይ ኮንግረስማኖች ድጋፋቸውን በመስጠት ፊርማቸውን አኑረዋል።

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ካለው የሰብአዊ አያያዝ ችግር ግር የአሜሪካ ኮንግረስም ሆነ አለም አቀፍ የመብት ድርጅቶች በአገዛዙ ላይ ተጽእኖ በመፍጠር የየበኩላቸውን ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።

በተለይም ካለፉት ሶስት አመታት ወዲህ በተከሰተው ሕዝባዊ አመጽ በርካታ ሰዎች መገደላቸውና መታሰራቸው ልዩ ትኩረትን ስቧል።

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ እስረኞችን በከፊል በመፍታት የአመራር ለውጥ በማድረግ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢመርጥም በሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ለውጥ ስለመኖሩ ግን ገና ማረጋገጫ አልተገኘም።

እናም እስካሁን የተፈጸሙ ወንጀሎች በገለልተኛ አካላት እንዲመረመሩና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር እንዲኖር ነገ ኤች አር 128 በአሜሪካ ኮንግረስ ድምጽ ይሰጥበታል ተብሏል።

ሕጉ እንዲጸድቅም በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩበት አካባቢ ለኮንግረስ ማኖች ስልክ በመደወል ተጽእኖ በማድረግ ላይ መሆናቸውም ታውቋል።

የ6ቱ የሰብአዊ መብትና የዲያስፖራ ቡድኖችም ሕጉ እንዲጸድቅ የመጨረሻ ጥረታቸውን በማድረግ ላይ ናቸው።

የዲያስፖራ ቡድኖቹና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በነገው ዕለት ድምጽ በሚሰጥበት ዋሽንግተን ዲሲ በመገኘት ድምጻቸውን እንደሚያሰሙም ለማወቅ ተችሏል።

2 Comments

  1. Thank you all caring for our voiceless and oppressed people. I strongly support HR 128 to approvefor tge sack of dying, prisoned,tortured innocent civilians and displaced millions people in there home land. Thank you all who helping us to pass HR 128 bill which allows Human Right Group to investigate the crime and abuse in Ethiopia and pushing the Ethiopian Government to work towards democracy Peace and stability to Ethiopia. Thank You.

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*