በመጨረሻም Hres128 ለድምፅ ሊቀርብ ነው

UNITED STATES - MARCH 19: House Budget Committee chairman Paul Ryan, R-Wisc., right, whispers to House Majority Whip Kevin McCarthy, R-Calif., during the House Republican leadership media availability after the House Republican Conference meeting in the basement of the Capitol on Tuesday, March 19, 2013. (Photo By Bill Clark/CQ Roll Call) (CQ Roll Call via AP Images)

HRes128 በሚቀጥለው ወር አፕሪል 9 ወይም አፕሪል 16 ሳምንት ላይ ለድምፅ አሰጣጥ እንደሚቀርብ የኮሎራዶው ተወካይ ማይክ ኮፍመን ዛሬ በላኩት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

 

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያውያን አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል ተወካይ ዲ .ዮሴፍ ይህ ለኢትዮጵያኖች ትልቅ ድል ነው ሲሉ ገልፀውታል።

ይሁን እንጂ ኮስፖንሰር ያላደረጉ በየስቴቱ ለሚገኙ የአሜሪካ ምክርቤት ተወካዮች መደውላችንን እስከ መጨረሻው መዘንጋት የለብንም ሲሉ ተናግረዋል። እንደሚታወቀው የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የአለም አቀፉ አጣሪ ቡድን እንዲገባ እንዲፈቅዱ የ28 ቀናት ጊዜ ገደብ ሰጥታ ነበር። የአሜሪካ ተሰናባች የውጭ ጉዳይ ስቴት ዲፓርትመንት ሃላፊ ቴሌርሰን በኢትዮጵያ ቆይታቸው ይህንን እንዲያደርጉ እና የጥምር መንግስት በአስቸኮይ እንዲመሰረት መንገራቸውንና ይህ ካልሆነ ግን አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን ግንኙነት እንደገና እንደምትመረምር አስጠንቅቀዋቸው ነበር። ይህን ለ Hres128 ለድምፅ መቅረብ ሰነ ስርኣት የውጭ የስቴት ሴክረተሪን  በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ያላቸውን ሃሳብ እንዲሰጡ ሲጠበቅ ነበር። በዚህም መሰረት የማጆሪቲው መሪ ኬቨን ማካርቲ የኢትዮጵያን ጉዳይ የሰበአዊ መበት ጥሰት የሚያየውን ረቂቅ ህግ ወደ ድምፅ እንዲቀርብ ዛሬ ወስነዋል።

3 Comments

  1. The time for Ethiopia is now. The God of Abraham, Isaac
    and Jacob can heal the wounds of our country. No matter how we do not think of Him in other times, when a family member gets sick and is in intensive care,
    we have access to His throne. Ethiopia is wounded and
    is in intensive care. This is the time to pray and intercede for mother Ethiopia remembering His love for
    our country whom we find her name in His holy book.

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*