በፍራንክፎርት የኢትዮጵያዊያን የነፃነትና እኩልነት ለኢትዮጵያ ግብረ ኅይል መግለጫ

በፍራንክፎርት የኢትዮጵያዊያን የነፃነትና እኩልነት ለኢትዮጵያ ግብረ ኅይል መግለጫ

በፍራንክፎርት የኢትዮጵያዊያን የነፃነትና እኩልነት ለኢትዮጵያ ግብረ ኅይል (Frankfurt Task Force Freiheit und Gerechtigkeit für Äthiopien) በወለደያ የጥምቀት እለት የወያኔ ወታደሮች በሰላማዊ የጥምቀት በዓል ኣክባሪ ፅላት የተሸከሙ የሃይማኖት ኣባቶች፤ እናቶቻችን፤ ኣባቶቻችን፤ እህቶቻችን፤ወንድሞቻችን በኣጠቃላይ በምዕመናኑ ላይ ካለምንም ምክንያት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተደረገውን ጭፍጨፋ በጥብቅ እያወገዝን ይህንንም ተከትሎ በቆቦ፤ ሮቢት፤ መርሳ ብሎም በኣጠቃላይ በኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው ኣሰቃቂ ፀረ ሕዝባዊ ጭፍጨፋን

ኣጥብቀን እያወገዝን፤ ይህንንም ኣረመኔያዊ  ጭፍጨፋ የጀርመን ነዋሪ ዜጎችም እንዲያውቁት ለተለያዩ የመገናኛ ጣቢያዎች እንዲያውቁትና እንዲያሳውቁም በኣባሪነት የላክነውን ፅሑፍ ያሳወቅን መሆናችንን እየገለፅን ውድ የቤተሰባቸውን ኣካል ለኣጡ የተሰማንን ሐዘን በመግለፅ ለቤተሰቦቻቸው፤ ለዘመዶችና ጓዳኞቻቸው መፅናናት እየተመኘን ኣሁን በዚህ ሰዓት በየእስር ቤቱ ኢሰበዓዊ በሆነ መንገድ በመንገላታት፤ በመሰቃየት ወዘተ ከምትገኙ የኣገር ሽማግሌዎች፤ ወጣቶችና ኣባወራዎች የትግል ኣጋርነታችንን እንገልፃለን።

 

ነፃነት፤ እኩልነት፤ ሕጋዊነት፤የሰፈነባትን ዲሞክራሲዊት ኢትዮጵያን በትግላችን እናዋቅራለን !!!

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!

read full in pdf

2018.02.01_Äthiopien 2222222

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*