የአሜሪካን የምክር ቤት አባላት የኢትዮጵያ መንግስት በውጪ የሚያደርገውን የኢንተርኔት ጠለፋ ክፉኛ አወገዙ!!!

የአሜሪካን የምክር ቤት አባላት የኢትዮጵያ መንግስት በውጪ የሚያደርገውን የኢንተርኔት ጠለፋ ክፉኛ አወገዙ!!!
የኢትዮጵያ መንግስት አለም አቀፋዊ ህግጋትን በመጣስ ስርአቱን ይቃወሙኛል ያላቸውን የሰበአዊ መብትና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያነጣጠረ የኢተርኔት ጠለፋን በአስቸኳይ ማቆም አለበት ሲሉ ተናገሩ።
በተለይም የአሜሪካው ምክርቤት የወታደራዊ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮንግረስምልን ማይክ ኮፍመን ለአሜሪካን ስቴት ዲፖርትመንት ሴክረቴሪ ቴሊርሰን ዛሬ በፃፉት ደብዳቤ መንግስታቸው ዝም ብሎ መመልከት እንደለለበት አሳስበዋል። የኢትዮጵያን አሜሪካን ዜጎችን ያነጣጠረ የመሰለል ስራ የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገ ነው ይህም ባለፈው ሲቲዝን ላብ የተባለው ኢንስቲትዩት ማጋለጡን ጠቅሰው በአስቸኳይ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል።
በተለይም በግዛቴ የሚገኝን የሰበአዊ መብት ተከራካሪ እና የኢትዮጵያን አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል አባል የሆነውን የአሜሪካን ዜግነት ያለውን ግለሰብ የኮሚውተር ጠለፋ መደረጉ እንዳሳሰባቸውና ጉዳዩን በቀላሉ እንደማያዩት በደብዳቤያቸው አስታውቀዋል።
አሜሪካን በዜጎቿ ላይ የሚደረግ ማናቸውንም ስለላ ትቃወማለች ያሉት ኮንግረስማን ማይክ ኮፍመን በጉዳዩ ላይ የዜጋቸውን የኢንተርኔት መብት የተጣሰ በመሆኑ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው እንደሚጠይቁ ታውቋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የስቴት ዲፖርትመንት ምን አይነት እርምጃዎችን እንደሚወስድ የታወቀ ነገር የለም።
እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ መንግስት በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያኖችን ያነጣጠረ ከቻይና እና ከጣሊያን መንግስት በገዛው የመሰለያ መሳሪያ ሶፍት ዌር ወይም ጋማ ተብሎ በሚጠራ ዘዴ የተለያዩ ኢሳትን ጨምሮ መጥለፉን በካናዳ የሚገኘው ሲቲዝን ላብ ባለፈው ወር ማጋለጡ ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፖለቲካ እስረኞችን እንፈታለን በሚለው የኢትዮጵያ መንግስት ዙሪያ:  H.res128 በኢትዮጵያ የሚደረገው እስራት እና ሰቆቃ እንዲቆም የሚጠይቀው የአሜሪካ ረቂቅ ህግ ለአደረግነው ውሳኔ ምንም ጫና አልፈጠረብንም ሲል የኢትዮጵያ መንግስት ቃለ አቃባይ ምላሽ ሰጥተዋል።

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*