የአሜሪካ ምክርቤት ለሰኞ ሊደረግ የነበረው የድምፅ ስነ-ስርአት ለሌላ ጊዜ መራዘሙን አስተባባሪዎቹ ገለፁ።

በአሜሪካ ምክርቤት ለሰኞ ሊደረግ የነበረው የድምፅ ስነስርአት ለሌላ ጊዜ  መራዘሙን አስተባባሪዎቹ ዛሬ ገለፁ።

ለኦክቶበር 2 , 2017 ሊደረግ የነበረው ኢትዮጵያን የሚመለከተው ህግ H.Res 128 መተላልፉን የኮንግረስ አባላት ዛሬ ለኮሚቴው አስታውቀዋል።

ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት የኢትዮጵያውያን አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል እና ኢትዮጵያን አድቮከሲ ኔትወርክ እንደገለፁልን ከሆነ የተላለፈበት ምክንያት በርካታ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው የአሜሪካ ነክ የሆኑ ጉዳዮች በእለቱ የተያዙ በመሆኑ ነው ሲሉ አስታውቀዋል።

በቀጣይ ቀናት ውስጥ መቼ ሊሆን እንደሚችል ከኮንገረስ ፅ/ቤት ጋር በመነጋገር እንደሚያሳውቁ በጠሩት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ የተጀመረው ዘመቻ H.Res 128 ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበትና ይህን ስራ ግብ ለማድረስ የኮንግረስ ባለስልጣናትን በስልክና በደብዳቤ ተሎ በአስቸኮይ ቀጠሮ እንዲያዝለት እንቅስቃሴ ማድረግ አለብን ብለዋል። ይህን ህግ እስከአሁን ስፖንሰር ያደረጉት ባለስልጣናት ከ70 ባላይ ገብተዋል

ይህ የሁላችን ጉዳይ ነው ያሉት አስተባባሪዎቹ ይህን ታሪካዊ ገጠመኝ በዲፕሎማሲው መስክ ውጤታማ ካደረግነው ለሃገራችንና ህዝባችን ድል ነው ሲሉ ገልፀዋል።

3 Comments

  1. Dear USA congress my name is Marta Getahun I am a citizen of USA but I am Ethiopian , I really concern about my people in Ethiopian, The government of in Ethiopian (TPLF) they are genocide Amhara and Oromo man and women young children every one there is no age limit with out any reason by heated those regions and taking there propriety also some of political activists & journalist abused in prison this kind of government they are happy to see people died,suffered and homeless as the human being I can’t see and I don’t want to have this kind of government in Ethiopian. The HR 128 may take quick actions to save my people. Thank you.

  2. ለሃገራችን እጅግ በጣም’ በጣም አስፈላጊ ነው:እና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የወገኔ ቢስት የኔነው የወገኔ ሞት ሞቴነው የአንድ ብኤር የበላይነት ይብቃ ኢትዮጵያ የሁሉም ቤኤር ናት የሚል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለዝህ ጉዳይ ቅድሚያ በመስጠት ድምፁን ለሚመልከተው በአሰቸዃይ ማሰማት አለበት ባይነኝ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*