የኢትዮጵያ መንግስት በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ እንደሚገኝ ዶ/ር አርአያ አምሳሉ ገለፁ

ዶ/ር አርአያ አምሳሉ ዛሬ ከኢሳት ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

ዶ/ር አርያ እንደተናገሩት H.Res 128  የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ በወያኔ መንግስት ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሮባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል። ለዚህም የወያኔ መንግስት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በማውጣት ሎቢስቶችን ቀጥሮ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል። አያይዘውም ይህን ረቂቅ ህግ በድል ለመወጣት ኢትዮጵያኖች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የተጀመረውን ዘመቻ ማጠናከር አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ መንግስት ልኡክ ቡድን በጠቅላይ ሚንስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ የተመራ የሁሉንም ክልሎች ፕሬዝዳንት በመያዝ የኦክልህማውን ሴነተር ጀምስ ኢንሆፍን አናግረዋል። ይህ ህግ እንዲቀርላቸውም ተማፅኖ ማድረጋቸውን አረጋግጠናል።

ጉዳዩን በተመለከተ ያነጋገርናቸው የአሜሪካን ተወካዮች እንደገለፁልን ከሆነ በአንድ ሴነተር ይህን በሙሉ ድምፅ ያለፈ ረቂቅ ህግን ለማስቆም አቅም አይኖራቸውም ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ከአሜሪካ ሴኔትና ኮንግረስ አባላት ጋር ተወያዩ

1 Comment

  1. The law HR 128 protect the Ethiopian people humaniterian ground. And expain the American Democracy for the world nation too. Bassed up this concept the current Ethiopian dectater Regime lobest for nothing westing the country Economee

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*