የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ እስረኞችን እፈታለሁ ሲል ማስታወቁን ተከትሎ በርካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው

የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ እስረኞችን እፈታለሁ ሲል ማስታወቁን ተከትሎ በርካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው::

የ H.Res 128 ስፖንሰር አድራጊው ኮንግረስማን ማይክ ኮፍመን እና የውጪ ጉዳይ ሰብሳቢው ኤድ ሮይስን ጨምሮ መግለጫ ያወጡ ሲሆን፤ መንግስት ቃሉን በተግባር ማሳየት ይጠበቅበታል ሲሉ ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥተዋል።

Coffman_Ethiopia_Jan.docx

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያን አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል ሰብሳቢ የሆኑት ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ ይህንን አስመልክተው ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ምልልስ ንፁሃን የሚሰቃዩበት የሚገርፉበት ሰቆቃን የሚቀበሉበት ማእከላዊ ብቻ ሳይሆን በርካታ ድብቅ እስር ቤቶች ስላሉ እውነት ይህን የሚያደርጉት እነዚህን ድብቅ እስርቤቶች ሁሉ ማፍረስ አለባቸው ብለዋል።


ዲ.ዮሴፍ ድርጅታቸው የጀመረውን የ H.Res128 እና Sen.Res 168 የሰበአዊ መብት መከበር በኢትዮጵያ እንዲኖር እና እስረኞችም እንዲፈቱ ህጉ ይጠይቃል። ይሁን እንጂ ይህ ጥያቄ  የሚጀምረው  1ሺ የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት ብቻ አይደለም በርካታ የፖለቲካና ጋዜጠኞች በእስር ቤት ተመዝግበው ይገኛሉ እነዚህን ሁሉ ማካተት አለበት ሲሉ ተናግረዋል::

የኢትዮጵያውያን አሜሪካን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ዜናው የሚበረታታ ቢሆንም በተግባር መረጋግጥ ይኖርበታል ሲል መግለጫ አውጥቶል::

https://amharic.voanews.com/a/4172750.html

 

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*