የH.Res 128 ሉእካን ቡድኑ የሰኞው ድርድር ውጤት ማምጣቱን ተናገሩ! ለኢትዮጵያ መንግስት የ28 ቀን ገደብ ተሰጥቶታል

የH.Res 128 ሉእካን ቡድኑ የሰኞው ድርድር ውጤት ማምጣቱን ተናገሩ! ለኢትዮጵያ መንግስት የ28 ቀን ገደብ ተሰጥቶታል!!

ሰኞ እለት ጃንዋሪ 29, 2018 የተደረገውን የH.Res 128 የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚመለከተው ረቂቅ ህግ ወደ ምክርቤት ቀርቦ ድምፅ እንዲሰጥበት በሚል የኢትዮጵያን አሜሪካዊያን ከኬቨን ማካርቲ እና በርከት ካሉ የህግ አውጭዎች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

በውይይታቸውም ለኢትዮጵያ መንግስት የ15 ቀን ገደብ መስጠታቸውን ዲ.ዮሴፍ ተፈሪ የቡድኑ አስተባባሪ በእለቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መናገራቸው የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ ይህን ተከትሎ የማጆሪቲ ሊደሩ ኬቨን ማካርቲ ለ H.Res128 ልኡካን ቡድን ትላንት በላኩት ደብዳቤ ይህ የጊዜ ገደቡ ተራዝሞ በፌውብራሪ 28, 2018 የኢትዮጵያ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ ካልወሰደ ረቂቅ ህጉን እንደሚያቀርቡት አረጋግጠዋል።  ይህንንም ትላንት ለኢትዮጵያ መንግስት ማሳወቃቸውን ጨምረው ኬቨን ማካርቲ ገልፀዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ሰብሳቢና መስራች ስለ ጉዳዩ ጠይቃናቸው የሚከተለውን መልስ ሰጥትውናል።

“ጉዳዩ በዚህ ፍጥነት መሰማቱና የተከበሩ ኬቨን ማካርቲ የኢትዮጵያውያን ድምፅ ሰምተው አስቸኮይ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን ማድነቅ እፈልጋለሁ” ካሉ በሆላ ለኬቨን ማካርቲ መልሰው ደብዳቤ በመላክ የፌውብራሪ 28, 2018 ን ገደብ ካውንስሉ እንደተቀበለው መልሰን ገልፀንላቸዋል ብልዋል ። ይህ ትልቅ ድል ነው ሲሉም አክለው ገልፀዋል። የ27 አመት የኢትዮጵያ እናቶች እንባ ሊሰማ የቀሩት ጥቂት ቀናቶች ናቸው እና አይዞችሁ ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያኖች አንድነታችንን በማጠናከር የጀመርነውን የዲፕሎማሲ ትግል መቀጠል አለብን። ይህ የሆነው በሁሉም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያኖች ርብርብ ነው ብልዋል ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ ። አሁንም ተጀመረ እንጂ እልጨረስንም ሩጫችን ያሉት ዲያቆን ዮሴፍ ኢትዮጵያኖች ስልክ በመደወል ኬቨን ማካርቲን ማመስገን እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ይህንን ጉዳይ በመላ አሜሪካ ለሚደረገው ዘመቻ የኢትዮጵያ አድቮከሲ ኔትወርክን በማግኘት ንቁ ተሳታፊ እንደንሆንም አደራ ብለዋል።

1 Comment

  1. This is a great job from both side. America must be awaken and stand beside the people of Ethiopia who are under repression. Woyane will have no moral and mental status to continue as a government. They became the real terrorist to their own people. Help for democracy. I would like to thank the group for such a tremendous effort. Great job! Keep going forward, we are with you. Thank you congressman Coffman. And thank you all other congressmen and respected bodies who supported this effort.

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*